የኮምፒውተር ትምህርት በአማርኛ
ደረጃ-1
አዘጋጅ፦ናኦድ ቤተሥላሴ
ይሄን ትምህርት ያዘጋጀሁት ኮምፒውተርን ለመጠቀም ጀማሪ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን በተለይ ደግሞ መሠረታዊ ኮምፒውተር ነክ እውቀት ስለጎደላቸው ብቻ ማይም የሆኑ ለሚመስላቸው ጠቢባን የቤተክርስቲያን አባቶቼ፤ ልጆቻቸውን ለማስተማር መማር ላልቻሉ ወላጆች እና እንጀራ ኮምፒውተር እና ኢንተርኔት እንዲማሩ ላስገደዳቸው ሀበሾች ነው። የማስተምረው ግን ኮምፒውተር ስለማውቅ አይደለም፤ ማካፈል ስለምወድ፤ እዚህ ስጠቅም እዛ እጠቀማለው ብዪ ስለማምን እንጂ።
በቀጣይ
ትምህርቶች ኮምፒውተርን ከማስጀመር እስክ ኢንተርኔትን ስለመጠቀም፤ አማርኛ ታይፕ ከማድረግ መልእክቶችን በኢሜል እና በስካይፕ ስለመለዋወጥ፤
በተያያዥም ከኮምፒውተር የማያንሰውን ስልካችን እና ቴሊቪዥናችንን አዛምዶ ስለመጠቀም በየደረጃው እንማራለን።
ትምህርቶቹ
ሲጠናቀቁ ተማሪዎች “ከጸሐይ በታች አዲስ ነገር የለም”፤ “የማይገለጥ የተከደን፤ የማይታወቅ የተሰወረ ነገርም የለም” ብለው ራሳቸው
በምፒውተራቸው መመራመር ይጀምራሉ ባይ ነኝ።
በአጭሩ፤
እኔ የጀመርኩትን ለመጨርስ ካደለኝ ወይም ተማሪዎች በርትተው ካጠኑ እና ከተለማመዱ ...
እናም
በትምህርቱ መጨረሻ (በግምት በ6 ወር ውስጥ) ተማሪዎች
1ኛ ለኮምፒውተር አጠቃቀም እንግዳ አይሆኑም
2ኛ. በኮንፒውተርኛ መነጋገር እና መጠየቅ ይችላሉ።
ለምሳሌ «ዴስክቶፕ ላይ ሴቭ የማደርገውን ፋይል ወደ ሌላ ፎልደር የማዘዋውረው እንዴት ነው? ... ብሎ እንደመጠየቅ
3ኛ. ወርድ በተባለው ሶፍትዌር ገጽ ላይ በአማርኛ
ታይፕ ማድረግ ይችላሉ
4ኛ. ስለ ኢንተርኔት ይረዳሉ፤ ኢሜይል ማድረግ እና ዩቲዩብን ስለመጠቀም ይማራሉ
5ኛ፦ ስልካቸው ላይ ያለውን ፎቶ እና ቪዲዮ ወደ ላፕቶፕ
ማዘዋወር እና ማየት ይችላሉ
6ኛ፦ ተጨማሪ እና ቀጣይ ትምህርቶችን በኢንተርኔት
ለመከታተል ብቁ ይሆናሉ።
7ኛ፦ መጨረሻ...የኮምፒውተርን አጠቃቀም ከባድ አድርጎ
ማሰብ አልችልበት ይሉና አላውቅም ማለት ይቸገራሉ። እንደ እኔ።እዚህ ላይ አውጣኝ በሉ!....
ናዖድ ቤተሥላሴ
አዘጋጁ
ናዖድ ቤተሥላሴ
አዘጋጁ
No comments:
Post a Comment