Thursday, January 14, 2016

1ኛ-ትምህርት-የኮምፒውተር ዓይነቶች፤ ክፍሎች እና አገልግሎታቸው

ዘወትር የምንገለገላቸው ኮምፒውተሮች ሁለት ዓይነት ናቸው። ዴስክ ቶፕ (Desk top) ይባላል። ሁለተኛው ዓይነት ደግሞ ላፕ ቶፕ (Lap top) ይባላል።

አንደኛው ዓይነት ዴስክ ቶፕ (Desk top) የሚለው የእንግሊዝኛ ህብረ ቃል ነው። ዴስክ- Desk- ማለት የቢሮ ጠርጴዛ ማለት ሲሆን ቶፕ- top- ማለት ደግሞ በአማርኛ አናት ወይም ራስ ወይም ከላይ ማለት ነው። ስለዚህም ዴስክ ቶፕ የሚለውን ቃል አቃንተን ስንተረጉመው ጠርጴዛ ላይ የሚቀመጥ ኮምፒውተር ነው።



   ሁለተኛው ዓይነት ደግሞ ላፕ ቶፕ (Lap top) ይባላል። ላፕ-Lap-ማለት ጭን ማለት ሲሆን ቶፕ- top ማለት ከላይ ማለት ነው። ስለዚሀ ላፕቶፕ ማለት ጭናችን ላይ አስቀምጠን የምንጠቀምበት ትንሽ ኮምፒውተር ነው።




ከዚህ በታች ባለው ስእል ላይ ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው ክፍሎች ስማቸው ወይም አገልግሎታቸው አንደ አይነት ነው።




ሞኒተር (Monitor)- እንደ ቴሌቪዥን መስሎ ኮምፒውተር ውስጥ የምንሰራውን ያሳየናል

ማውስ (Mouse) ወይም የላፕቶፕ ተች ፓድ (touch pad) መጠቆሚያ ሲሆን ኮምፒውተሩ እንዲሰራ የምንፈልገውን ነገሮች በመጠቆም ትዕዛዝ የምንሰጥበት ነው።

 ኪቦርድ (Keyboard) ፊደላት እና ቁጥሮችን የያዙ ቁልፎች የተደረደሩበት ሰሌዳ ነው። አገልገሎቱም ኮምፒውተር ውስጥ ጽሑፎችን ለመጻፍ ነው።

ሲፒዩ (ሴንተራል ፕሮሰሲንግ ዩኒት ወይም ሲስተም ዩኒት) የኮምፒውተር ማሰቢያ፤ ማሰላሰያ፤ ማእከል ነው።

ኮምፒውተርን በሰው አምሳያ ብንመለከተው ሲፒዩ እንድ ጭንቅላት፤ ኪቦርድ እንድ ጣቶች፤ ማውስ እንድ ጠቋሚ ጣት፤ ሞኒተር ደግሞ እንድ ዓይን ሆኖ ኮምፒውተሩ የሚሰራውን የሚያሳየን ነው። ከዚህ በተጨማሪ ኮምፒውተር ድምጽ የሚያወጣበት ስፒክር፤ ድምጽ የሚቀዳበት ማይክሮፎን፤ የመሳሰሉ ጠቃሚ ክፍሎች አሉት።







No comments:

Post a Comment