ቀሪው ትምህርታችን
የሚያተኩረው በ ላፕቶፕ ላይ ነው። ምክንያቱም በዚህ ዘመን ዴስክ ቶፕ በብዙ ግለሰቦች ዘንድ እምብዛም ስለማይገኝ ወይ ጥቅም ላይ
ስለማይውል።
ላፕቶፕን ማብራት
ማለት ልክ የመኪናን ሞተር እንደማስንሳት ማለት ነው። መኪናው ሞተሩ ስለተነሳ ይሄዳል ማለት አይደለም፤ ለመሄድ ተዘጋጅቷል ማለት
እንጂ። ላፕቶፕንም ስናበራ ላፕቶቡ ሞተሮቹን ለስራ እንዲያዝጋጅ ማንቃት ማለት ነው።
ላፕቶፕን ለማብራት
ከኪቦርዱ በላይ የሚገኘውን የፓወር ቁልፍን መጫን ነው።
የፓወር ኪ (Power Key=ፓወር ኪ=የማብሪያ
ማጥፊያ ቁልፍ ቁልፍ)፡በሚከተለው ዓርማ ይታወቃል።
ላፕቶፕ ሲጀምር
ሞኒተሩ ላይ ስዕል መታየት ይጀምራል። ላፕቶፑን የሚጠቀመው ሰው ፓስ ወርድ (ፓስ ወርድ =Password= የምሥጢር ኮድ ) ታይፕ እንዲያደርግ የሚጠይቅ ገጽ ይከፈታል። ለምሳሌ
የእኔን ላፕ ቶፕ ሳስጀምር ምን እንደሚመስል በስዕል ሁለት ላይ ይመልከቱ።
ይህንን ሲያዩ ኢንተር የሚባለውን ቁልፍ ከ ኪቦርድ ላይ ይጫኑ። ኢንተር የሚባለው ኪ ይህንን
ይመስላል።
ስዕል3፦ኢንተር የሚባለው
ቁልፍ
ኢንተር ስንጫን ወድ ተጠቃሚ ማንነት ማረጋገጫ ገጽ እንገባለን
ስዕል4፦የኮምፒውተር ተጠቃሚ
ማንነት ማረጋገጫ ገጽ
ብልህ ላፕቶፕ ሥራውን
ዝምብሎ አይጀምርም። መጀመሪያ የሚያገለግለውን ሰው ማንነት ማረጋገጥ ይፈልጋል። ስለዚህ በስዕል 4 ላይ የተመሰለውን ጥያቄ ይጥይቃል።
1ኛ ጥያቄ= ይህ ፎቶ ወይም ምስል የአንተ ነው? ታውቀዋለህን? የሚል ትርጉም ያለው ፎቶግራፍ
ያሳያል። ባለቤቱ ፎቶ ካላስቀመጥ ግን ምንም ፎቶ አያሳይም። ለምሳልይ እኔ ላፕቶፔ ላይ «ፎቶዮ» ነው ብዮ የሰጠሁት ልጆች ቤተክርስቲያን
የሚማሩበት ትምህርት ቤት ዓርማ ነው። የእኔ ላፕቶፕም «ፎቶዮ ነው» ያልኩትን አምኖ መቀበል እንጂ ከእውነተኛ መልኬ ጋር ማመሳከር
አይችልም።
2ኛ ጥያቄ= ስምህ ማን ነው? እዚህ ላይ «ስምህ» ሲል፤ ለእኔ የነገርከኝ ስም ማለቱ እንጂ
እውነተኛ ስምህን ማለቱ አይደለም። የኮምፒውተሩ ባለቤት ወይ ተጠቃሚ
ላፕቶፑን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጠቀም ስሜ ነው ብሎ የመዘገበውን «ስምህ» ነው ብሎ ይመዘግበዋል። ከዚያ ሌላ ጊዜ ባለቤቱ ወይ ተጠቃሚው
ሰው ላፕቶፑን ለማስጀመር ሲል፤ በማንነት ማረጋገጫ ገጽ ላይ አስቀድሞ የመዘገባቸውን የተጠቃሚ ስሞች እና ፎቶግራፎች ያሳያል። እኔ
ነኝ ያል ፎቶውን መርጦ ክሊክ (ክሊክ=Click= ተች ፓድን በጣት ሲጫኑት የሚሰማ «ቀጭ» የሚል ድምጽ ነው። ተች ፓድ ምን እንድሆን
ከላይ በስዕል 2 ላይ አጥንተናል አይደል?
3ኛ ጥያቄ= የሚስጥር ቁልፍህ (ፓስ ወርድ) ምንድን ነው። በሳጥኑ ውስጥ ታይፕ አድርግ (ጻፍ)
4ኛ ጥያቄ= ይህንን ቀስት ምልክት ተጫን ወይም ኪ ቦርድህ ላይ ኢንተር የሚለውን ቁልፍ ተጫን።
አራቱን ጥያቄዎቼን በትክክል ከመለስክ ላፕቶፕ እንድትጠቀም እፈቅድልሃለሁ። ከተሳሳትክ እንደገና ጥያቄዎቹን በትክክል ለመመለስ ሞክር።
አለዚያ ላፕቶፕ መጠቀም አልፈቅድልህም።