(This is a suppliment for a classroom lesson on How to...youtube.)
ዩቲዩብ የሚባለው ድረገጽ
ማንኛውም ዓይነት ቪዲዮዎችን በነጻ የምናይበት፤ የራሳችንንም ቪዲዮዎች በነጻ የምንጭንበት እና ለሰዎች የምናካፍልበት አንድ መድረክ
ነው። ዩቲዩብን ለማየትም ሆን ቪዲዮዎችን ለመጫን ኢንተርኔት ሊኖረን ያስፈልጋል። በአሁኑ ዘመን ስልኮቻችን ኢንተርኔት ስላላቸው፤
ዩቲዩብ ላይ ያሉ ቪዲዮቻችንን በስልካችን ማየት እንችላለለን። በስልካችን የቀረጽነውንም ቪዲዮ ዩቲዩብ ላይ ያንኑ ስልክ ተጠቅመን
መጫን እንችላለን። ቪዲዮዎችን ማየት ኢንተርኔት ያለው ሰው ሁሉ ቢችልም፤ የግል ቪዲዮቻችንን ዩቲዩብ ላይ ለመጫን እና ለሰዎች ለማካፈል
ግን የሚችሉት የጉግል ኢሜይል አካውንት ማለትም @ጂሜይል ዶት ኮም የሚል አድራሻ ያለው ኢሜይል ያላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው።
ከዚህ በታች ያለው ቪዲዮ፤
በክፍል ውስጥ የተለማመድነውን የዩቲዩብ አጠቃቀም በአጭሩ የሚያሳይ ነው። በፊልሙ ላይ፤ 1ኛ፦ የዩቲዩብን ድረ ገጽ እንዴት እንደምናገኝ፤
2ኛ፤ ካገኘን በኋላ የምንፈልገውን ቪዲዮ እንዴት እንደምናገኝ 3ኛ፤ ቪዲዮችን ስንመለክት ደግሞ የቪዲዮን ድምጽ እንዲተ እንድምንቆጣጠር፤
ወይም ቪዲዮውን ከመጫወት እንዲያቆም ወይም መልሶ መጫወት እንዲጀምር ስለምናደርግበት ዘዴ እንመለከታለን። በቀጣይ ተያያዥ ትምህርቶች
ደግሞ ተጨማሪ የድረገጽ ሙያዎችን እንማራለን።
No comments:
Post a Comment