ኢ-ሜይል (e-mail) የሚለው ቃል የእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃል ሲሆን የእንግሊዝኛው
ሙሉ ቃል ኤሌክትሮኒክ ሜይል (electronic mail) የሚል ነው። e-በሚል ፊደል ያሳጠርነው electronic የሚለውን ቃል ነው።
እንግሊዝኛ
|
አነባበብ
|
ትርጉሙ
|
electronic
|
ኤሌክትሮኒክ
|
በኤሌትሪክ
ቴክኖሎጂ የሚሰሩ ኮምፒውተሮች፤ ስልኮች ወዘተ..
|
mail
|
ሜይል
|
መልዕክት
|
ኢ-ሜይል የሚለውን ቃል በቀጥታ ሲተረጎም በኤሊትሪካዊ መንገድ የሚላግ የፖስታ መልዕክት ማለት ነው። በኤሌትሪካዊ መንገድ
የሚለው ቃል ግን የሚያመለክተው ኮምፒውተርን እና ስልኮችን ነው። ስለዚህ ኢ-ሜይል የሚለውን ቃል አቃንተን ስንተረጉመው ኮሚፒውተር
እና ስልክን በመጠቀም መልክቶችን በኢንተርኔት የምንላላክበት መንገድ ነው ልንል እንችላለን።
የእኛ
ፖስተኛ
እና
የኮምፒውተር ፖስተኞች
የኢ-ሜይልን አስራር እና አጠቃቀም ለመረዳት ኮምፒውተር አዋቂ መሆን አያስፈልግም።
ምክንያቱም ማንም
·
ለዘመድ ለወዳጆቹ ወይ ጉዳይ ለሚፈጽሙ መስሪያቤቶች
·
በ ነጭ ወረቅት ደበዳቤ ጽፎ፤
·
ለማስታወሻ ወይም ማስረጃ እንዲሆን ደግሞ ፎቶ ግራፍ ወይ ስነድ ከደብዳቤው ጋር አባሪ ያደረግ
·
ማሽጊያ ፖስታ ላይም
o
ላኪ ብሎ ስሙን የጻፈ
o
ተቀባይ ብሎ የተቀባይን ስምና አድራሻ የጻፍ
·
ፖስታውን ፖስታ ቤት ሂዶ የስጠ ሰው
·
የመለስ ደብዳቤ እንደመጣለትም ፖስታ ቤት ሄዶ የፖስታ ሳጥኑን የከፈተ
·
ወይም ደግሞ ፖስተኛ በሩን አንኳክቶ ፖስታዎችን በበሩ ቀዳዳ የተቀበለ ሰው ሁሉ የኢሜይልን
አስራር ለመረዳት አያዳግተውም። ኢሜይል በኮምፒውተር ስለሆን እንጂ አሰራሩ እንዲሁ ነውና።
ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ፤ በተለይ እዚህ አሜሪካ የሚኖር ሰው፤ ፖስተኛ በበሩ ቀዳዳ የሚወረውርለት ወይም በሳጥኑ ውስጥ የሚያስቀምጥለት
ፖስታዎች ሁሉ ቁም ነገር እንዳልሆኑ ያየ ሰው፤ በኢሜይል የሚደርሱት መልኤክቶች ሁሉ ጠቃሚ እንዳልሆኑ ለማወቅ አያዳግተውም። ፖስተኛ
የሚሰጠን ፖስታዎች
·
ሁሉም የተቀባይ ስም በሚለው ቦታ የእኛ ትከከለኛ ስም እና አድራሻ አላቸው። ይዘታቸው ግን
ለየቅል ነው።
o
አብዛኛው ማስታወቂ ነው
o
ጥቂቱ ደግሞ ማጭበርበሪያ መልእክቶች፤ በውሸት ገንዘብ እንድንልክላቸው የሚፈልጉ ናቸው
o
ከአስር አንዱ ደግሞ ስንጠብቀው የነበር የዘመድ ወዳጅ ደብዳቤ ወይም ወርኃዊ የመብራት እና
ወሃ ክፍያ ሰነዶች ናቸው።
በኢሜይልም የሚደርሱን መል እክቶች ጠባያቸውም ሆን ይዘታቸው እንዲሁ ነው። ሁሉም የሚላኩልን በስማችን እና በአድራሻችን
ነው፤ ይዘታቸው ግን ለየቅል ነው።
ዋናው ጥንቃቄ፤ ላኪውን ካላወቅነው ኢ-ሜይሉን አለመክፈት፤ ከከፈትነውም ውስጡ ያያዛቸውን ስ እሎች እና አባሪ ነገሮች አለመነካካት
ነው። አንዳንዶቹ መዘዛቸው ኮምፒውተራችንን ወይም ስልካችንን ከማበላሽት እስክ የባንክ እና የግል ኢንፎርሜሽናቸነነ እስክ መዝረፍ
ይደርሳልና።
ከዚህ በታች ያለው ሠንጠረዥ የወረቀት ፓስታ እና ኢሜይልን ዝምድና እና ልዩነት በአጭሩ ያሳያል
ማወዳደሪያ ነጥቦች
|
ፖስታ
|
ኢሜይል
|
·
የላኪ ስም ይጻፋል?
|
አዎ
|
አዎ
|
·
የተቀባይ ስም ይጻፋል?
|
አዎ
|
አዎ
|
·
ቴምብር ያስፈልጋል?
|
አዎ
|
አያስፈልግም
|
·
ገንዘብ ያስከፍላል?
|
አዎ
|
አያስከፍልም
|
·
አባሪ አድርጎ ፎቶግራፍ ለመላክ ያስችላል?
|
አዎ
|
አዎ
|
·
አባሪ አድርጎ ቪዲዮ ለመላክ ያስችላል?
|
አይችልም
|
አዎ
|
·
አባሪ አድርጎ ቁሳቁስ ለመላክ ያስችላል?
|
አዎ
|
አይችልመ
|
·
|
||
·
ፖስተኛው እንዴት ይላካል?
|
በሰው፤ በመኪና፤በአየር
|
በኢንተርኔት
|
·
ፖስታ ላኪ እና አቀባይ መስሪያ ቤት ስሙ ማን
ነው?
|
ፖስታ ቤት
|
ጉግል፤ያሁ፤አውትሉክ
|
·
ፖስታ ቤቱ የት ነው?
|
አንድ ህንጻ ውስጥ
|
ኮምፒውተር፤ስልክ
|
·
የተላከልን ፖስታ በስንት ጊዜ ይደርሳል?
|
ከፈጠን 3 ቀን
ከዘገየ...ወራት
|
ከፈጠን 3 ሰክንድ
ከዘገየ 15 ደቂቃ
|
·
ሩቅ ሀገር መልዕክት በመላክ አንጻርs
|
ዋጋው ይወደዳል
ጉዞውም ይዘገያል
|
ርቀት አይወስነውም
ፍጥነቱም ብዙ አይለያይም
|
·
አድራሻው በትክክል የተጻፈበት ፖስታ አልደረሰኝም
ብሎ መካድ ይቻላል?
|
አዎ
|
አይቻልም
|
·
ለእኔ የተላከ ፖስታ ሌላ ሰው ጋ ሊደርስ፤ ወይም
ያልፈቀድኩለት ሰው ፖስታዮን ከፍቶ ሊያነበው ይችላለ?
|
አዎ
|
አይችልም
|
·
ፖስታ ለመላክ እና ለመቀበል ስሜን?
|
የለብኝም
|
አለብኝ
|
·
የፖስታ አድራሻ ምን ይመስላል?
|
Naod Beteselassie
1000 Our Street Washington, DC 20900 |
naodbete@gmail.com naodbete@yahoo.com naodbete@outlook.com |
·
የመጣልኝን ፖስታ ለማግኘት የፖስታ ሳጥን ቁልፍ መያዝ አለብኝ?
|
የለብኝም
|
አለብኝ
|